አዲስ ቻምበር በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ ለተሰማሩ አባላቱ በኩባንያ መልካም አስተዳደር ምንነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰልጠና ተሰጠ ፡፡

የአዲስ ቻምበር የዳሬክተሮች ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው ይህ ሰልጠና ቀደም ሲል ለባንክ አመራሮችና የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት ሲሰጥ የነበረው ሰልጠና ቀጥሎ ነው የተሰጠው ፡፡
ሰልጠናውን የሰጡት ጥላየ ካሳየ ( ፒ.ኤች.ዲ) ንግድ እንዲቀጥልና ዘላቂ እንዲሆን በጥሩ መሰረት ላይ መጣል አለበት አለበት ፤
ከዚህ ውስጥ አንዱ መሰረት የኩባንያ መልካም አስተዳደር መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡
የኩባንያ መልካም አሰተዳደደርን በተመለከተ ገለፃ ሲያደርጉ ፤ አንድ ድርጅት ፖሊሲዎች ፣ ህጎች ፣ ደንቦች ሊኖሩት ይገባል ያሉት ጥላየ ( ፒ.ኤች.ዲ) ይህም ድርጅቱ ውስጥ ያሉትን ሰራተኞች እንዲሁም ከውጭ ያሉ የተለያዩ አካላት ለማገናኝት የሚያስችል መሳሪያ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡
በመሆኑም ግንኙነቶችን የተሳለጠና ውጤታማ በማድረግ የኩባንያው አሰተዳዳሪዎች ወይንም እነሱን የሚወክሉ ሰዎች ያለውን ሰርዓት ፣ ህግ እና ፖሊሲ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሊያውሉ ይገባል ብለዋል ፡፡
አክለውም ኩባንያዎች የኩባንያ መልካም አስተዳደርን በድርጅቶቻቸው ውስጥ ቢተገብሩ ዘረፈ ብዙ ጥቅም ያጋኛሉ ያሉት ጥላየ ካሳሁን ( ፒ.ኤች.ዲ) ፤ የኩባንያ መልካም አስተዳደርን መተግበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ኩባንያ እንዲሆን ያስችለዋል ፡፡
ሌላው የንግድ ድርጅቶች በደንበኞቻቸው ፣ በምርት አቅራቢዎቻቸው እንዲሁም በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተቀባይነት ሲያገኙ የማደግ እድላቸው ከፍተኛ እንዲሆን ማድረግ ሌላኛው እንደሆነ አንሰተዋል ፡፡
በመሆኑም በኩባንያ መልካም አስታደደር መርህ ተከትሎ የሚመራ ኩባንያ እድገቱ እና ትርፋማነት ብሎም የመስፋፋት እድሉ ከፍተኛ የማድረግ እድል አለው ብለዋል ፡፡
ይሁንና የኩባንያ መልካም አሰተደደርን ተግባራዊ የማያደርጉ የቢዘነስ ድርጅቶች ባለህበት እርገጥ በማድረግ በሂደት መወዳዳር ሰለማይችል ከገቢያ ሊወጣና ብሎም ሊከሰም የሚችልበት እድል የሰፋ መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡
ይህም የሚመነጨው ድርጅቱን የሚመሩ አካላት አቅምና ችሎታ አለመኖር አንዱ ሲሆን ለኩባንያ መልካም አስተዳደር ያላቸው እይታ ትክክል አለመሆኑን በዋናነት አንሰተዋል ፡፡
ድርጅቱን በሚመሩ አካላት ፣ ባለድርሻ አካላት እና የቦርድ አባላት መካከል የሚፈጠር አለመስማማትና መጠላለፍ ለኩባንያ መልካም አሰተዳደርን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት የሚያበላሽ መሆኑን አንሰተዋል ፡፡
በኢትዮጰያ የኩባንያ አስተዳደርን እንዳይተገበር ዋነኛ ችግር ሆነው ከሚቀመጡት መካከል የኩባንያ መልካም አሰተዳደር ሚናን አለመረዳት ፣ በቂ በጀት አለመመደብ እንዲሁም በባለአክሲዮኖች እና ኩባንያውን በሚመሩ የስራ ኃላፊዎች መካከል መልካም ግንኙነት አለመኖር መሆናቸውንም ጥላየ ካሳሁን ( ፒ.ኤች. ዲ) ጠቅሰዋል ፡፡
ያ ማለት በኢትዮጵያ የኩባንያ መልካም አሰተዳደር ደካማ ነው ብሎ መደምደም አይቻልም ያሉት ጥላየ ( ፒ.ኤች. ዲ) ብሄራዊ ባንክ ከሚሰጠው ጠንካራ የቁጥጥርና ክትትል አሰራር የተነሳ የባንክ ዘርፉ ትርፋማ መሆኑን አንሰተዋል ፡፡
ይህም ሊሆን የቻለበት ባንኮቹ ባላቸው ማኔጅመንት ብቻ ሳይሆን የኩባንያ መልካም አሰተዳደር ሰራቸው ጠንካራ በመሆኑ ነው ብለዋል ፡፡
በመሆኑም ይህንን የኩባንያ መልካም አሰተዳደር በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲሰፋፋ አዲስ ቻምበር የጀመረውን እንቅሰቃሴ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡
በተለይ አሁን ላይ ብዙ ኩባንያዎች እና ኢንቨሰተሮች ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ መሆኑን ጠቁመው ንግድ ምክር ቤቱ የጀመረውን እንቅሰቃሴ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ፡፡