የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከተለያዩ የንግድ ተቋማት ተወካዮች ጋር በኢ-ኮሜርስ (የበይነመረብ ግብይት) እድሎች እና ተግዳሮቶች በሚል ርእስ ውይይት አካሒዷል።
ማህበረሰቡ የምርቶችን ጥራት እና ጥንካሬ በአካል አረጋግጦ የመሸመት የግብይት ባህል ያለው በመሆኑ በኢ-ኮሜርስ የሚኖር ሽያጭ ላይ እምነት ያለመኖር ችግር እንዳለም ጠቁመዋል ።
የአፍሪኮም ቴክኖሎጂ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ዘይኑ በበኩላቸው በሀገሪቱ ከ50 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ተጠቃሚዎች መኖራቸው እንዲሁም ገና ያልተነካ ዘርፍ መሆኑ እንደ እድል የሚታይ መሆኑን ገልጸው ከመድረኩ እንደ ችግር የተነሱትን ጨምሮ የተማረ የሰው ሀይል እጥረት እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንዛቤ በበቂ ሁኔታ አለመኖር ተግዳሮቶች እንደሆኑ ጠቅሰዋል ። የግሉ ዘርፍ በንቃት እና በፍጥነት በኢ-ኮሜርስ ላይ ተሳትፎ የማያደርግ ከሆነ ፍላጎት ያሳዩ እና አቅም ያላቸው የውጭ የበይነመረብ አገበያዮች ቁጥጥር ስር እንደሚውል ገልጸዋል ።
እንደ አሊባባ እና አማዞን ያሉት ታዋቂ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በኢ-ኮሜርስ ለመሰማራት ፍላጎት አሳይተዋል። አቶ ባህሩ መንግስት የሚጠበቅበትን ሀላፊነት መወጣት እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል። ነገር ሀገር በቀል ኩባንያዎች ችግሮችን ተቋቁመው በመስራት በዘርፉ ራሳቸውን ማብቃት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።