የንግዱ ህብረተሰብ ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራውን አሳረፈ

የአዲስ ቻምበር አመራሮችና ሠራተኞች በእንጦጦ ተራራ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አስተባባሪነት አዲስ ቻምበርን ጨምሮ የኦሮሚያና የሸገር ከተማ የንግድ ምክር ቤቶች በእንጦጦ ፓርክ በመገኘት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የዘንድሮውን አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የንግዱ ማህበረሰብ ወኪል የሆኑትን ንግድ ምክር ቤቶች ማሳተፍ ችሏል፡፡

በዚህ መርሀ ግብር ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሀላፊ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፤ የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕረዚደንቶች እና የቦርድ አመራሮች እንዲሁም ከፍተኛ የማኔጅመነት አባላትና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ በሁሉም አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር የተስተካከለ እና ዘላቂነት ያለው ሥነ ምኅዳር ለመፍጠር ፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግ፣ የግብርና ምርታማነትን ለመጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም ፤ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታን እና የከተማ ውበትን ለማሻሻል የጎላ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ብሎ አዲስ ቻምበር ያምናል ፡ ፡

አጠቃላይ የአዲስ አበባ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ በዚህ ጠቃሚ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ላይ በስፋት በመሳተፍ እና የሚተክላቸውንም ችግኞች በመንከባከብ ታሪካዊ እና ሀገራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አዲስ ቻምበር ጥሪ አድርጓል።

#addischamber