አዲስ ቻምበር ለሲኒየር ባለሙያዎችና የማኔጅመንት አባላት የአመራር ክህሎትን ማሳደግ የሚያስችል ሰልጠና ሰጠ

አዲስ ቻምበር ለሲኒየር ባለሙያዎችና የማኔጅመንት አባላት የአመራር ክህሎትን ማሳደግ የሚያስችል ሰልጠና ሰጠ ፡፡

በከፍያለው ዋሲሁን
‹‹Growth mind set for leadership effectiveness›› በሚል ርዕስ ለ40 የምክር ቤቱ ሰራተኞች ክህሎቶቻቸውን ማዳበር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ነው ሰልጠናው የተሰጠው ፡፡

የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሀፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም ንግድ ምክር ቤት 77 ዓመት ማስቆጠሩን አስታውሰው ፤ ንግድ ምክር ቤቱ ለአባላቱ ለሚሰጠው አገልግሎት መቀላጠፍ ለውጥ እና እድገት ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

የ SAK ቢዝነስ እና ፐርሰናል ዲቨሎፕመንት መስራችና ስራ አሰኪያጅ አደራ አብደላ ( ፒ.ኤች.ዲ ) በሰጡት ስልጠና በተሰማራንበት ስራ ውጤታማ ለመሆን አመለካከት ለውጥ ማምጣት ይገባል ብለዋል፡፡

እንደ ባህል ፣ እምነት ፣ ማህበረሰብ ፣ ትምህርት እና አካበቢ የልቡና ወቅር ( ማይንድ ሴት ) የሚቀርፁ መሆናቸውን ጠቅሰው ፤ይህንን መቀየር ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

በመሆኑም የንግድ ምክር ቤቱ ስራተኞች በስራቸው ስኬታማ እንዲሆኑ መማርና መሻሻል ላይ ትኩረት ማድረግ ፣ ጠንክሮ መስራት ፣ ዲስፕሊን እና መልካም ልማድን ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል ፡፡

የድርጅቶች ውድቀትና መነሳት ካላቸው እቅድና ግብ በተጨማሪ ስራተኞች እራሳቸውን ለፈታኝ ስራዎች እጅ ሳይሰጡ ጠንክረው በመስራት የልቦና ውቅር በማሳደግ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ገልፀዋል ፡፡

በስልጠናው ላይ የተገኙ የምክር ቤቱ ሰልጣኞች ባገኙት ስልጠና መደሰታቸውን ገልፀው አደራን( ፒ.ኤች.ዲ) አመሰግነዋል ፡፡