አዲስ ቻምበርና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በግሉ ዘርፍ ልማት ዙሪያ በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መከሩ ፡፡

የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድና የቦርድ አባላቱ ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የግዢና የሎጀስቲክስ የስራ ቡድን ሊቀመንበር ሚስተር አሊ አሳድ እና ሌሎች አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚስተር አሊ በውይይታቸው እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት በሚያወጣቸው የአገልግሎትና የእቃዎች ግዢና ጨረታ የከተማይቱ የንግድ ህብረተሰብ ይበልጥ ተሳታፊ እንዲሆን ከአዲስ ቻምበር ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል ፡፡

ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በበኩላቸው አዲስ ቻምበር በኮሚሽኑም ሆነ በሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች የሚወጡ የግዢ ፍላጎቶች መላው የንግዱ ህብረተሰብ አቅራቢ የሚሆንበትን ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል ፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በግንቦት 15፤2025 በሚያካሄደው የቢዝነስ ኮንፈንስ ላይ አዲስ ቻምበር ስትራቴጂካዊ አጋር እንዲሆንም ጥሪ ቀርቧል፡ ፡

ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በግሉ ዘርፍ እድገት ላይና መሰል የቢዝነስ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡