ንግድ ም/ቤቱ ለሠራተኞቹ በፖሊሲ አድቮከሲ ዙሪያ  ሥልጠና ሰጠ

በይድነቃቸው ዓለማየሁ

የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት ከተቋቋመበት ዓላዎች መካከል ለአባላቱ እና ለመላው  የንግድ ሕ/ብ  ምቹ የንግድ ምሕዳር አንዲፈጠር ንግድ ነክ የሆኑ የፖሊሲ ሕጸጾችን ነቅሶ በማውጣት በመንሥት የፖሊሲ ማሻሻያዎች አንዲደርግባቸው የአድቮከሲ ሥራዎችን ማከናወን አንዱ ነው፡፡

ይህን ግንዛቤ በመውሰድ ከካናዳ በመጡ ከፍተኛ ባለሙያ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የአድቮኬሲ ስልጠና ተሰጥቷል፤፤

ሥልጠናው ሠራተኞች  የሚያገለግሉትን የንግድ ሕብረተሰብ ስለ ሚመለከቱ  የፖሊሲ  ጉዳዮች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው እንዲሁም በሥራቸው ላይ የነጋዴውን ጥቅምና መብት ማስጠበቅ ታሳቢ እንዲያደርጉ ያግዛል ተብሏል፡፡

ለ10 ቀናት የሚቆየው ሥልጠና  ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ከፍተኛ ባሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን  ስልጠናውም በአድቮከሲ ፅንሰ-ሐሳብ፤መሠረታዊ መርሆች፤ የአድቮኬሲ አተገበባር ሰልቶች፤የባለድርሻዎች ሚና፤ የአድቮከሲ ስትራቴጂ አዘገጃጀት፤የፖሊሲ አቋም ሰነዶች አዘገጃጀት  እንዲሁም የአገራት የአድቮከሲ ልምዶች ላይ  ያተኩራል፡፡

ንግድ ም.ቤቱ  ካታሊስት ፕላስ ከተባለ የካናዳ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሥልጠናውን በትብብር እንዳዘጋጀ  ለመረዳት ተችሏል፤፤