እ.ኤ.አ. ከኦገስት 13-16፤ 2ዐ25 ዓ.ም. ድረስ በቱርክ ኢስታንቡል በሚካሄደው የአለም የኢንዱስትሪዎች ትብብር ፎረም/ World Cooperation of Industries Forum (WCI) እና የንግድ ለንግድ ውይይት መርሀግብር ላይ ከ30 በላይ የአዲስ ቻምበር አባላት እና የንግድ ልኡካን ቡድን ተሳታፊ ናቸው፡ ፡
በአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ የተመራው የንግድ ልኡክ ከቱርክ እና ከሌሎች ሀገራት ባለሀብቶች ጋር የገበያ ትስስር የሚፈጥርበት መርሀ ግብር እንደተመቻቸለት ከፕሮግራሙ መረዳት ተችሏል፡ ፡
በፎረሙ መክፈቻ ላይ የተለያዩ አገራት ሚኒስትሮች እና ትላልቅ የንግድ ኩባንያ አመራሮች ተሳትፈዋል፡ ፡
ፎረሙና የንግድ ለንግድ ውይይቱ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ ይፈጠርበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፤
በኢስታንቡል እየተካሄደ የሚገኘው ፎረም ከ1‚5ዐዐ በላይ የንግድ ተቋማትን የሚያሳትፍ ሲሆን የአዲስ ቻምበር አባላትን ጨምሮ ከአፍሪካ እንዲሁም ከተለያዩ አገራት የተውጣጡና በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ የቱርክ እና ሌሎች ሀገራት ኩባንያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡