ለአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አባላት በሙሉ

አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ/ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል(በቀድሞው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል) ከጠዋቱ 2፡3ዐ ጀምሮ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምከር ቤት ፕሬዚዳንት፣ ም/ፕሬዚዳንትና የቦርድ አባላት ምርጫም ይካሄዳል፡፡ ይህ ምርጫ ግልጽና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከፍተኛ ልምድና የሥራ ፍላጐት ያላቸው አባላት የሚገኙበት የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡
ኮሚቴው ለፕሬዚዳንትነት፣
ለም/ፕሬዚዳንትነትና ለዲሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታዎች የሚጠቆሙትን ዕጩዎች ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አባላት ለዕጩዎች በወጣው መስፈርት መሠረት ለተጠቀሱት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ራሳችሁንም ሆነ ብቃት ያላቸውን ሌሎች አባላት እንድትጠቁሙ ጥሪ እናቀርባለን፡፡