ፓፓያን አቀነባብሮ/ አድርቆ/ እና አበልጽጎ ለገበያ የማቅረብ እድል ሰፊ መሆኑ የአዲስ ቻምበር ጥናት ጠቆመ::

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ፓፓያ በማምረት 5ኛ ብትሆንም በምርት ሂደት 30 በመቶው የባክናል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፓፓያን አበልጽጎ እና አቀነባብሮ/አድርቆ/ ለገበያ በማቅረብ ዙሪያ በሚኖሩ እድሎችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ጥናት አስጠንቶ ባለድርሻዎች እንዲወያዩበት አቅርቧል፡፡

በውይይቱ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት የተወከሉ ባለድርሻዎች፣በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች ተሳትፈውበታል፡፡

በጥናቱ እንደተጠቆመው ፓፓያ ባለው ጠቃሚ ንጥረ ነገር የምግብ እጥረት ችግርን ለመፍታት የሚያግዝ ቢሆንም የምርት ሂደቱ የዘመነ ባለመሆኑ እና ምርቱ ወቅት ላይ የተገደበ በመሆኑ ከዘርፉ ሊገኝ ይችላል ተብሎ የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት እንዳልተቻለ ተጠቁሟል፡፡

በሃገራችን ፓፓያን አድርቆ በተለያየ አይነት ለገበያ የሚያቀርብ እና ወቅት ሳይጠበቅ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያደርግ የአግሮ ኢንዱስትሪ ባይኖርም ጥናቱ ሌሎች ፍራፍሬዎችን በማቀነባበር ዘርፍ የተሰማሩት ላይ የሚታየውን ተግዳሮቶች የዳሰሰ እና በፓፓያ ዘርፍም ሊከሰት የሚችል መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በጥናቱ ላይ የደረቅ ፓፓያ ዘርፍም ይገጥሙታል ተብለው ከቀረቡት ተግዳሮቶች መካከል፣ የአቅርቦት ችግር፣ የምርት ግብአት ውድ መሆን፣ ዝቅተኛ የግብአት ጥራት፣ የውጭ ምንዛሬ እጦት እና ባንኮች የግብርና ምርትን ባህሪ የተረዳ የፋይናንስ ስርአት አለመከተላቸው እና ሌሎችም የዘርፉ ተግዳሮቶች ሲል ጥናቱ አስቀምጧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *