አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በኢንተር-ሌግዠሪ ሆቴል (በቀድሞው ኢንተርኮንትኔታል ሆቴል) ሐሙስ፣ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ያካሂዳል፡፡
ጉባኤው የ2012፤የ2013 እና የ2014 በጀት ዓመት የሥራ ክንውንን ይገመግማል፡፡ የውጭ ኦዲተሮች የሚያቀርቡትን ሪፖርት መርምሮ ያፀድቃል፤ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት፣ ም/ፕሬዚዳንትና የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫም ያከናውናል፡፡
ጉባኤው የንግዱን ኅብረተሰብ መብትና ጥቅም ለማስከበር የሚያስችሉ ሀሳቦች የሚፈልቁበት መድረክ በመሆኑ የሁሉም የምክር ቤቱ አባላትን ንቁ አስተዋጽኦ የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም የእርስዎ በጉባኤው ላይ መገኘት ለምክር ቤታችን የወደፊት እርምጃ እጅግ ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን፡፡
ስለሆነም በዚህ ጉባኤ ላይ የድርጅትዎ ሥራ አስኪያጅ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም ሐሙስ ከጠዋቱ በ2፡30 ሰዓት ጀምሮ በአዲሱ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ተገኝተው በጉባኤው ላይ እንዲሳተፉ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ቢሆን፣ ለዚሁ የተዘጋጀውን የውክልና ደብዳቤ የያዙ የድርጅትዎን ባልደረባ መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ከማክበር ሰላምታ ጋር