ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መኖሩ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯልም ተባሏል፡፡
የውጭ ምንዛሬን ሙሉ በሙሉ ለገቢያው ክፍት ማድረግ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤትን/ድብልቅ ውጤትን/ ሊያስከትል እንደሚችል ተነግሯል ፡፡
ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባዛጋጀውና የውጭ ምንዛሬን ገቢያው እንዲወሰነው ክፍት ማድረግ እና የሌሎች አገራት ተሞክሮ ምን ይመሳላል በሚል በቀረበ ጥናት ላይ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የተለያዩ የንግዱ ማህበረሰብ ችግሮችን በጥናት ላይ በመመሰረት የአድቮኬሲ ስራ ይሰራል ፡፡
በጥናቱ ከውጭ ምንዛሬ ሰርዓቱ ጋር በተያየዘ ፅንሰ ሃሳቦች ምን ይላሉ ፣ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ነፃ ያደረጉ የተለያዩ አገራት ተሞክሮ ምን ያሳያል ፣ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያለው የውጭ ምንዛሬ ሁኔታ ፣ ገቢያው ነፃ ሲደርግ በንግድ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ተዳሷል ፡፡
የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ሊፈጠር የቻለበት የተለያዩ ምክንያቶች አንዳሉ የጠቀሱት ጥናት አቅራቢውና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ኢያሱ ኩመራ የወጪ ንግድ አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆን ፤ የሃብት ሽሽት ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ ጦርነት እና ሌሎችም ለምንዛሬው እጥረት አስተዋፆ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት፣ የብሄራዊ ባንክ አንዳንድ ህጎች ፣ የዋጋ ንረት እና ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚላከው ገንዘብ በባንኮች በኩል አለመላክ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን እንዲባባስ ምክንያት መሆናቸውን አቶ እያሱ ኩመራ ጠቁመዋል፡፡
ታዲያ አሁን ላይ የሚታየውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ በእርግጥም የምንዛሬ ገቢያውን መክፍት አንዱ አማራጭ ሊሆን እንደሚችል አንስተዋል ፡፡
አቶ አያሱ አክለውም የተለያዩ አገራት የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን ነፃ ማድረጋቸውን ጠቅሰው የአገራትን ተሞክሮ ለማሳየነት አቅርበዋል ፡፡
የምንዛሬ ገቢያውን ነፃ ያደረጉ አገራት የሚፍልጉትን ውጤት አስገኝተዋል ወይ የሚለውን በጥናታችን አይተናል ያሉት አቶ እያሱ አብዛኞቹ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ያንን እውን ማድረግ አለመቻላቸውን ነው የገለፁት ፡፡
የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ነፃ ካደረጉ በኃላ አገራት የዋጋ ንረት ፣ የንግድ ሚዛን ጉድለት በመፍጠር የማክሮ ኢኮኖሚ አለመረጋጋት እንደገጠማቸው ጥናቶችን ዋቢ አድርገው ጠቅሰዋል ፡፡
እንደ ጥሩ ተሞክሮ የሚወሰደው የኢስያ ሀገራት መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ ሀገራት ውስን በሆነ ደረጃ ገቢያውን ከፍት ማድረጋቸው ውጤታማ መሆናቸውን ጠቅሰዋል ፡፡
ሰኬታማ ሊሆኑ የቻለበት ምክንያት አንዱ ገቢያውን አንዴ ከመከፈት ይልቅ ቀስ በቀስ ( ግራጁሊዝም ) መንገድን መከተላቸው ፣ እወቀት መር መንገድን መከተላቸው ፣ ጠንካራ የማዕከላዊ ባንክ ያላቸው መሆኑ እና የትኛው መቅደም አለበት የሚለውን አካሄድ መከተላቸው ነው ብለዋል ፡፡
በአፍሪካም አስር የሚሆኑ አገራትን በተሞክሮ ለማሳየነት በጥናቱ መመልከታቸውን የጠቀሱት አቶ እያሱ ፤ እነዚህ አገራት የውጭ ምንዛሬውን ነፃ ከማድረጋቸው በፊት ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ገልፀዋል ፡፡
ሀገራቱ ከፍተኛ የሚባል የዋጋ ንረት ፣ የንግድ ሚዛን መዛባት ፣ የጥቁር ገቢያ መስፋፋት ፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችት በከፍተኛ ሁኔታ የወረደበትና መሰል ችግሮች ይስተዋል እንደነበረ ጠቅሰዋል ፡፡
በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅርፍ የውጭ ምንዛሬ ገቢያው እንዲመራው በሚል ነፃ ማድረጋቸው ድብልቅ የሆነ ነገር መፍጠሩን ጠቁመዋል ፡፡
መጀመሪያ አካባቢ ላይ ችግር እና አለመረጋጋት ቢኖርም በሂደት ወደ መረጋጋት መምጣቱን አመላክተዋል ፡፡
ሆኖም በቀጣይ የዋጋ እና የምንዛሬ መጠን መረጋጋት እንደመጣ ፣ የወጪና ገቢ ንግድ መጠንን እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ክምችታቸውን ማሳደደግ ችለዋል ፡፡
የውጭ ምንዛሬ የገቢያ ሰርዓቱን ነፃ ያደረጉ ሀገራት መካከል የተሳካላቸው እንዳሉ ሁሉ ሰኬታማ ያልሆኑ አገራት መኖራቸውንም ጠቁመዋል ፡፡
ኬኒያ ፣ ዩጋንዳ መጀመሪያ አካበቢ ላይ ችግር ቢገጥመውም በሂደት መረጋጋት ችሏል ፡፡ ከኢሲያ ሀገራት መካከል ቻይና እና ደቡብ ኮሪያ ቀስ በቀስ ገቢያውን ነፃ ማድረጋቸው የተሳካ ገቢያን እንዲፈጠር እንዳስቻላቸው ተጠቅሷል ፡፡
ጋና እና ናይጀሪያ የውጭ ምንዛሬ ገበያን ነፃ ቢያደርጉም ውጤቱ ግን የሚፈለገውን አይነት አልነበረም ፡፡
በተለይ ናይጄሪያ የወጪ ንግዷ አነሰተኛ መሆንና የገቢ ምርት ላይ የተንጠለጠለች መሆኗ ውጤታማ መሆን አለመቻሉን ገልፀዋል ፡፡
ሱዳንም የውጭ ምንዛሬ ሰርዓቷን ገቢያ መር አድርጋው አምሳ አመት ብትሰራበትም ውጤታማ መሆን አለመቻሉን ተከትሎ እ. ኤ.አ በ1993 ነፃ መሆኑን አንሰታለች ፡፡ በአንፃሩ ሩሲያ እና ኡዝቤክስታን የውጭ ምንዛሬ ገበያቸውን በአንዴ ክፍት ማድረጋቸውን ተከትሎ ሰኬታማ መሆን እንደተሳናቸው አቅርበዋል ፡፡
ሌላኛው የጥናት አቅራቢ አቶ መላኩ ታንኩ በበኩላቸው በሀገሪቱ በመደበኛ ማለትም በባንክና በጥቁር ገበያ መካከል ልዩነት መስፋት አንደኛው ብሄራዊ ባንክ የሚቆጣጠረው መሆኑ ነው ብለዋል ፡፡
በተጨማሪም የውጪ ምንዛሬ በወረፋ እና በሰልፍ የሚገኝ በመሆኑ ፍላጎቱን ማሟላት እንዳልቻለ እና የጥቁር ገቢያውንም እያሰፋው እንደሆነ ጠቁመዋል ፡፡
ታዲያ የውጭ ምንዛሬውን ከመክፈታችን በፊት የዋጋ ንረት አሁን ካለበት መቀነስ ፣ የወጭ ንግድ ግኝታችንን ማሳደግ ፣ የክፍያ ሚዛን መስተካከል እና፣ የብሄራዊ ባንክ የቁጥጥር አቅም መጠናከር አለበት ብለዋል ፡