የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አብሮ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ በግሉ ዘርፍ እና በመንግስት ትብብር ንግድና ኢንቨስትመንትን ይበልጥ ለማስፋፋት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን አቅም በማስተባበር የከተማዋን የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች በሀገር ውስጥና በውጪ ለማስተዋወቅ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
ሁለቱም ተቋማት የጋራ እቅድ በማውጣት ስምምነቶቹን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ በፊርማ ስነስርአቱ ወቅት ተገልጿል፡፡