የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ ከራሺያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ለመጡ ዓለም አቀፍ የቢዝነስ ትብብር አባላት በኢትዮጲያ እና በአዲስ አበባ ስላሉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ አደረገ፡፡ የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሃፊ አቶ ጌታቸው ረገሳ በሀገሪቱ ስላለው የግል ዘርፍ ሁኔታና እምቅ አቅም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በውይይቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡