የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ለበርካታ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን የኢፍጣር መርሐ-ግብር በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል በመገኘት አካሄዱ።

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት(አዲስ ቻምበር) ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሐመድ የረመዷንን ጾም ምክንያት በማድረግ በራሳቸው ተነሳሽነት ለበርካታ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች የኢፍጣር መርሐ-ግብር በመቄዶንያ አካሂደዋል ፡፡

ፕሬዝዳንቷ እንደገለፁት አዲስ ቻምበርም ሆነ መላው የንግዱ ሕብረተሰብ በተለያየ መልኩ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በቻለው አቅም ከጎን በመሆን ማህበራዊ ሀላፊነቱን አጠናክሮ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል ።

በኢፍጣሩ  ላይ የተገኙት የማእከሉ መስራች አቶ ቢኒያም በለጠ ለምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት በአረጋዊያን እና በህሙማኑ ስም ምስጋና አቅርበው አዲስ ቻምበር እና አባላቱ ባለሀብቶች እንዲህ ያለውን የማህበራዊ ሀላፊነት የመወጣት ስራ በዘላቂነት እንዲወጡ በአክብሮት ጥሪ አቅርበዋል ።

wpChatIcon
wpChatIcon