የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የቦርድ አመራሮችና ሰራተኞች የምክር ቤቱን 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና የሀገር አቀፍ አረንጓዴ አሻራ የችግኝ መርሃግብር ምክንያት በማድረግ ስድስት ዓይነት ዝርያ ያላቸውን ሀገር በቀል ችግኞች በእንጦጦ ተራራ ተክለዋል ፡፡
“ንግድ ምክር ቤታችን ችግኝ መትከልን እንደ ህልውና ጉዳይ ይወስደዋል፤ የንግድ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን ለመከላከልና እንደዜጋ ለቀጣይ ትውልድ አሻራውን ለማኖር ተሳትፎውን ሊያጠናክር ይገባል፡፡”
ወ/ሮ መሰንበር ሸንቁጤ ፣ የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት
“ይህ ችግኝ ተከላ ንግድ ምክርቤታችን ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከቀረፀው የክረምት ፕሮጀክት መካከል አንዱ ነው፤ በከተማችን ንግድ ምክር ቤቱን ሊወክል በሚችል ቦታ ላይ የአረንጓዴ አሻራ ልማት እንክብካቤ ላይ ለመሳተፍ ሰፊ ስራ ይሰራል፡፡ ”
አቶ ሺበሺ ቤተማርያም፣ የአዲስ ቻምበር ዋና ፀሐፊ
“የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ተሳታፊ ሆኜ አሻራዬን ለማኖር በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፤ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም አለብን ”
ወ/ሮ ናርዶስ አማረ ፣ የአዲስ ቻምበር ሰው ሃብት ልማትና ሎጆስቲክ መምርያ ስራ አስኪያጅ
“በችግኝ ተከላው መርሃግብር የራሴን አሻራ አስተዋፅኦ በማድረጌ በጣም ደስ ብሎኛል ”
ወ/ሮ ሚስጢር መሃመድ፣ የምክርቤቱ ከፍተኛ የህግ ባለሙያ::