ኤግዚቢሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት በ2015 በጀት ዓመት በማዕከሉ ለተዘጋጀው የአደይ እንቁጣጣሽ 2015 ኤግዚቢሽንና ባዛር ትልቁን ድርሻ ለወሰዱት ተቋማት በማዕከሉ ቅጥር ግቢ የዕውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ::
በዕውቅና አሰጣጡ ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ታደሰ፤
የአደይ እንቁጣጣሽ 2015 ኤግዚቢሽንና ባዛር ስኬታማነት አስተዋጾ ላበረከታቹ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በ2015 በጀት ዓመት ለነበራችሁ አስተዋጽኦና ዕውቅና ስንሰጥ አብሮነታችን በቀጣይ ጊዚያቶች እንደሚቀጥል ተስፋ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ለባለድርሻ አካላት እና ድጋፍ ላደረጉ አካላት የዕውቅና የምስክር ወረቀት ከልዩ ማስታወሻ ጋር ተሰጥቷቸዋል፡፡
በዕውቅና ፕሮግራም ላይ የአዲሰ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ኘሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ; የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ጸሀፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም እና ዕውቅና የተሰጣችው አካላት ተሳትፈዋል፡፡