ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችና አምራቾች በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚገጥማቸውን የተወዳዳሪነት ተፅዕኖ ለመቀነስ ንግድ ምክር ቤቶችና መንግስት የቤት ስራ አለባቸው ተባለ ፡፡

ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችና አምራቾች በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚገጥማቸውን የተወዳዳሪነት ተፅዕኖ ለመቀነስ ንግድ ምክር ቤቶችና መንግስት የቤት ስራ አለባቸው ተባለ ፡፡

ከፍያለው ዋሲሁን

የአዲስ ቻምበር ባዘጋጀውና << Maximizing Opportunities in AfCFTA >> በሚል በተካሄደው ሰልጠና ላይ በቀረበ ፁሁፍ ላይ ነው ፡፡

የመወያየ ፁሁፍን ያቀረቡት የህግ ባለሙያና በዓለም አቀፍ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር አማካሪ የሆኑት አቶ ወንድወሰን ሽዋረጋ እንዳሉት የአፍሪካ አህጉር ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ለኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች እድልም ፈተናም ይዞ የሚመጣ ነው ብለዋል ፡፡

ለኢትዮጵያዊያን ቢዝነሶችና አምራቾች ይዞት ከሚመጣው ጥቅም አንዱ በ53ቱ የአፍሪካ አገራት ምርቶቻቸውን ያለምንም የቀረጥ ክልከላ ይዘው እንዲገቡ ማስቻሉ እንደሆነ ጠቅሰዋል ፡፡

ሁሉም ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስራቸውን በማሳደግ በጋራ እንዲበለፀጉ የሚያስችል እድል ይፈጥራል ሲሉ አቶ ወንደወሰን ተናግረዋል ፡፡

ይህ ማለት ግን ነፃ የንግድ ቀጠናው እድል ብቻ ሳይሆን ፈተናም ይዞ እንደሚመጣ ሊታወቅ ይገባል ያሉ ሲሆን የአገር ውስጥ አምራቾች እራሳቸውን የማብቃት ስራ ከወዲሁ ካልሰሩ ከሌሎች አገራት በሚመጡ ምርቶች ከፍተኛ ውድድር ሊገጥማቸው እንደሚችል ገልፀዋል ፡፡

አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት ተመሳሳይ ምርት የሚያመርቱ መሆኑን አቶ ወንድወሰን ጠቅሰው ፤ ይህ ደግሞ ነፃ ንግድ ቀጠናው እውን ሲሆን በአገር ውስጥ አምራቾች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል ፡፡

የነፃ ንግድ ቀጠናው ለመተግበር ከአጠቃላይ 8ሺ የምርትና ቢዝነስ አገልግሎቶች መካከል 97 በመቶ የሚሆኑት ከቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ አገራት የተሰማሙባቸው ናቸው ብለዋል ፡፡

ለዚህም 13 ዓመታት የድርድርና የመዘጋጃ አመታት አስቀምጣል ቀሪ 3 በመቶ ምርቶች ደግሞ ሀገራት ቀረጥ እንዲጥሉባቸው ስምምነቱ ላይ መቀመጡን ተናግረዋል ፡፡

በመሆኑም 13 ዓመታት የመሽጋገሪያ ጊዜ መኖሩን ጠቅሰው ፤ ይህንን ጊዜ ምርታማነታቸውን ማሻሻልና አቅማቸውን ሊያጎለብቱበት ይገባል ብለዋል ፡፡

ውድድሩ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ላይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ቢዝነሶች ወደ ሌሎች አፍሪካ አገራት ምርቶቻቸውን ለመላክ ከወዲሁ ዝግጅት ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁመዋል ፡፡

ከወዲሁ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ካዘጋጀናቸው ከነፃ ንግድ ቀጠናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመስራት ሊገጥማቸው ከሚችል ፉክክር አሽነፈው እንዲወጡ ማድረግ ይቻላል ብለዋል ፡፡

ታዲያ ንግድ ምክር ቤቶችና መንግስት ኢትዮጵያዊያን አምራቾችና ላኪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል ፡፡

ይሁንና የቤት ስራው ለመንግስትና እንደ አዲስ ቻምበር ላሉ ንግድ ምክር ቤቶች ብቻ የሚተው ሳይሆን የንግድ ማህበረሰብ በራሱ ውድድሩን አሽንፎ ለመውጣት እራሱን ሊያዘጋጅ እንደሚገባ አቶ ወንደወሰን ነግረውናል ፡፡

ዝግጀቱ በፋይናንስ ፣ በሰው ኃይል አቅም በመገንባት ፣ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ከወዲሁ ተወዳዳሪ በመሆን ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አቶ ወንደወሰን እምነታቸውን ገልፀዋል ፡፡

ኢትዮጵያ ከቀረጥ ነፃ የሚደረጉና ቀረጥ የምታስከፍልባቸውን የመደራደሪያ ምርቶችን ለአፍሪካ አህጉር ነፃ ንግድ ቀጠና ፅ/ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት ለነፃ ንግድ ቀጠና ፅኅፍት ቤት ማስገባቷ ተነግሯል ፡፡

ይሁንና የትኞቹ ምርት ከቀረጥ ነፃ ተደርጉ ፤ የትኞቹ ምርትቶችና አገልግሎቶች ናቸው ቀረጥ የሚጣልባቸው የሚለውን በተመለከተ መንግስት ያለው ነገር የለም ፡፡

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና በ2018 ሩዋንዳ ላይ የተፈረመ ሲሆን ፤ ከኤርትራ በቀር 53ቱ የአፍሪካ አገራት ስምምነቱን ተቀብለው ማፀደቃቸው ይታወሳል ፡፡