Responsible Business Conduct(RBC) በተዛማጅ ትርጉሙ ኃላፊነት ስሜት የሚታይበት ንግድ አካሄድ አንደማለት ነው፡፡
መሠረታዊ ዕሳቤውም ነጋዴው ሕብረተሰብ የንግድ አንቅስቃሴውን በሚያደርግበት ወቅት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሰውን እና አካባቢን ከሚጎዱ ማንኛውም ድርጊቶች አንዲቆጠብ የሚያሳስብ ነው፡፡
በአገራችን የዚህ ዘመናዊ የንግድ አሰራር መርሆች አገራችን በተቀበለችው ዓለማቀፍ ሕግጋት፤በተለያዩ አዋጆች እና ደንቦች ላይ ተካትተዋል፡፡
ነገርግን ንግድ ምክር ቤቱ የንግዱን ሕብረተሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ ተከታታይ ስልጠናዎች እየሰጠ ነው፡፡
ዛሬ ላይ የዓለማቀፉ ንግድ ሥርዓት የ RBC መርሆዎች ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጥባቸው የውድድር መስፈርቶች አንዱ እየሆነ መጥቷል፡፡
ስለዚህ የአገራችን ኩባንያዎች ዓለማቀፍ ተወዳዳሪ ሆነው አንዲገኙ ፤ከውጪ ኩባያዎች ጋር ዘላቂ የንግድ ትስስር መመሥረት አንዲችሉ ፤ ከትላልቅ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና መሥራት አንዲችሉ ከወዲሁ ንግዳቸውን የRBC መርሆዎችን በድርጅታቸው አሰራር ውስጥ ማካተት አለባቸው፡፡
RBC ለኩባንያዎች ከሚሰጠው ጥቅሞች መካከል አገር ውስጥ ኩባንያዎች ሰለሸሪኮቻቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁ፤ በሕግ ፊት መብት እና ግዴታቸውን አውቀው አንዲንቀሳቀሱ፤ በደንበኞቻቸው ዘንድ ዘላቂ ታማኝነት እና መልካም ዝና አንዲያተርፉ አንዲሁም በአጠቃላይ ቢዝነሳቸው ዘመን ተሻጋሪ እና ለትውልድ የሚተላለፍ እንዲሆን ይረዳል ሲሉ ስልጠናውን የሰጡት ወ/ሮ ጺዮን አድማሱ ተናግረዋል፡፡
ንግድ ምክር ቤቱ ከዴኒሽ ኢንደስትሪ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሥልጠና አባል ኩባንያዎቹ ይህንን ዘመናዊ የንግድ አመራር እንደ የሥራ ፀባያቸው አስማምተው ተግባራዊ እንደያደርጉ ድጋፍ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡