(ነሃሴ 12፣2012) የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ ምላሾችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ምክር ቤቱ በኮቮድ 19 ምክንያት ተጋላጭ እና ተጎጂ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የዚህ አንድ አካል የሆነው ማእድ የማጋራት ፕሮግራም ሽሮሜዳ ለሚገኙ 150 ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች እና በኮቪድ ምክንያት ገበያ ላጡ ሸክላ ሰራተኞች የመጀመሪያውን ዙር 150 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ የምግብ እና የዘይት ምርቶችን በመስጠት ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ሞክሯል፡፡
በቀጣይም በልደታ እና በአራዳ ለሚገኙ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመድረስ እቅድ ይዟል፡፡
በቀጣይም የሽክላ አምራቾቹ ዘላቂ በሆነ ሁኔታ የሚደገፉበትን እና ምርታቸው በዘመናዊ መልኩ የሚያመርቱበትን መንገድ እንደሚመቻች የንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤቱን ፕሬዚዳንት ጨምሮ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትና ማኔጅመንቱ እንስራ ተባለውን የሸክላ ማእከል ጎብኝተዋል፡፡