ንግድ ምክር ቤቱ በመሠረታዊ ኮሚኒኬሽን እና በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ስልጠና ሰጠ::
በይድነቃቸው ዓለማየሁ
በስልጠናው የውስጥ እና የውጪ ተቋማዊ ተግባቦት/ኮሚኒኬሽን ሥራዎች የሚመሩባቸውን መሰረታዊ መርሆች፤ደንቦች ፤ የሚያስከትሉት ተጠያቂነት እና ሃላፊነቶች እንዲሁም የአገራት ልምዶች ተዳስሰዋል ፡፡
ስልጠናው ለአዲስ ቻምበር የማኔጅመንት እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሰጥቷል፡፡
የዓለም ንግድ ሥርዓት እጅግ ፈጣን እና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በሚታዩበት በዚህ ዘመን ስልጠናው አዲስ ቻምበር ለአባላቱ ወቅታዊና ተአማኒ የቢዝነስ መረጃዎች መስጠት ያስችለዋል ተብሏል ፡፡