የኩባንያ መልካም አሰተዳደር ለገቢያ መር ኢኮኖሚ በተለይም ለፋይናንስ ብሎም ለአጠቃላይ የንግድ ከባቢ አዎንታዊ አስተዋፆ ያበርክታል ብለዋል ፡፡
አቶ ሰለሞን አክለውም በኮርፖሬት ቢዝነስ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ጠንካራና ሚዛኑን የጠበቀ የዳሬክተሮች ቦርድ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል ፡፡
በአግባቡ የሚመሩ ኩባንያዎች ከፍተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ዓላማቸውን እንዲያሳኩ እንደሚያስችላቸውም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ፡፡
ታዲያ ይህንን ለማሳካትና የአንድን ኩባንያ አስፈፃሚ አመራሮችን ለመቆጣጠር ተወዳዳሪና ብቃት ያለው የዳሬክተሮች ቦርድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በተለይ በግሉ ዘርፍ ያለውን የኩባንያ አመራር ከተለምዷዊ አሰራር በማውጣት የዳሬክተሮች ቦርድ አመራር የኩባንያ መልካም አስተደዳር በማዘመን ፣ በባለሙያ እንዲመራ በማድረግ የአዲስ ቻምበር አመራሮች የሰጡትን ጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነት አድንቀዋል ፡፡
አክለውም ንግድ ምክር ቤቱ ያቋቋመው የዳሬክተሮች ኢንስቲትዩት ለቦርድ አባሎቻችን ፣ ቦርድ ስባሳበቢዎችን ፣ ስራ አስፋፃሚዎችና የቢዝነስ አመራሮች ዘንድ ለውጥ ለማምጣት ልምድ የሚካፈሉበትና የሚወያዩበት በመሆኑ ከፍተኛ ቦታ እንደሚሰጡት ተናግረዋል ፡፡
የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሽንቁጤ በበኩላቸው በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ የአመራር ሚናዎች መካከል የዳሬክተሮች ቦርድ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል ።
ለአንድ ድርጅት እድገት የቦርድ ዳሬክተሮች ካላቸው ከፍተኛ ህጋዊ ኃላፊነት በተጨማሪ ፤ ድርጅታዊ ባህሪን ብሎም ባህልን በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ አክለዋል ፡፡
ንግድ ምክር ቤታቸው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር አደዲስ አገልግሎቶችን በመቅረፅ መጠነ ሰፊ ማሻሻያ እያደረገ ይገኛልም ብለዋል ፡፡
በዚህም አዲስ ቻምበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የዳሬክተሮች ኢንስቲትዩት በይፋ ስራ ማስጀመሩን አስታውቀዋል ፡፡
ንግድ ምክር ቤቱ አድማሱን በማስፋት ጠንካራ፣ ብቁ ባለሙያ እና ባለራዕይ የዳይሬክተሮች ቦርድ መገንባት ላይ አትኩሮ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡edited 19:16