ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ‹‹ የብድር አቅርቦት በግሉ ዘርፍ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ››የሚዳደስስ የውይይት መድረክ ላይ ነው ፡፡
የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሽንቁጤ መድረኩን ሲከፍቱ እንዳሉት የግሉ ዘርፍ ችግር ብሎ ካስቀመጣቸው መካካል የብድር አቅርቦት አለመኖር 40 በመቶ ድርሻ ይይዛል ::
አክለውም የገንዘብ አቅርቦት ፣ከውጭ ምንዛሬና ብልሹ አሰራር በመቀጠል በሶስተኝነት ደረጃ ላይ መቀመጡን ጠቅሰው ፤ ይህም ችግሩ ምን ያህል ስር የሰደደ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል ፡፡
በፋይናንስ አቅርቦት ላይ ያሉ ችግሮች የግሉ ዘርፍ አዳዲስ ምርት ለማምረትና ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ማነቆ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ ከብሄራዊ ባንክ ፣ ልማት ባንክ ፣ አዋሽ ባንክ የተገኙ ባለሙያዎች የብድር አቅርቦት ላይ ያሉ ምቹ እና አሰቻይ ሁኔታዎች እንዲሁም ፈተናዎች በመዳሰሰስ በቀጣይ ምን መሰራት አለበት የሚለውን አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል ፡፡
ከብሄራዊ ባንክ የመጡት አቶ በለጠ ፎላ የብድር አቅርቦት ለሁለንተናዊ አገር አድገት እድገት ያለውን ፋይዳና ከፖሊሲ አንጻር ያሉ ምቹ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው ፤አስቻይ ሁኔታዎችስ አሉ ወይ የሚለውን ዳሰዋል ፡፡
ከብድር ጋር በተያየዘ ያለውን ፖለሲ ሲያብራራ ቀደም ሲል የብድር አሰጣጡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ብቻ እንደ ዋስትና ያደረገ እንደነበር አውስተዋል ፡፡
ይህም በመሆኑ የሚያስይዙት ንብረት የሌላቸው ሰዎች ብድር እያገኙ አለመሆናቸውን ጠቅሰው ፤ አሁን ላይ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች እንደ ብድር ዋስትና የሚታዩበት ሁኔታ መፍጠሩን ገልፀዋል ፡፡
ቀደም ሰል ከፍተኛውን የብድር መጠን የሚያቀርቡት ንግድ ባንክና እንዲሁም የፖሊሲ ባንክ የሆነው ልማት ባንክ ብቻ ከፍተኛ መጠን ያለውን ብድር ያበድሩ አንደነበር አስታውሰዋል ፡፡
ሆኖም የግሉ ዘርፍ የማበደር ድርሻ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰዋል ፡፡
ይሁንና የብድር ተደራሽነቱን በተመለከተ ሀገሪቱ ካላት 120 ሚሊየን ህዝብ ውስጥ የበድር ተጠቃሚ መሆን የቻሉት 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ሰዎች ናቸው ብለዋል ፡፡ይህም የሚያሳየው የብድር ተደራሽነት ዝቅተኛ መሆኑን ነው ብለዋል ፡፡
ለብድር አቅርቦቱ ማነስ ፈተናው ከራሳቸው ከባንኮች አሰራር እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር በተያየዙ ችግሮች እንዳሉ አንስተዋል ፡፡
በችግርነት ከተቀመጡት መካከል ብድር ከወሰዱ በኃላ የመክፍል ፍላጎት መቀዛቀዝ አንዱ ሲሆን ፤ የፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ የተበላሽ የበድር መጠን ከፍተኛ ነው ብለዋል ፡፡
በተጨማሪም የበድር የወለድ መጠን እና የአገልግሎት ክፍያ ከፍተኛ መሆን ፣የውጭ ምንዛሬ እጥረት ዋና ዋና ችግሮች መከካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል ፡፡
ከአፍሪካ የፋይናንስ ግልፀነትና ተጠያቂነት የመጡት አቶ ጌታቸው ተ/ማርያም በበኩላቸው በግሉ ዘርፍ የብድር ተጠቃሚነት ላይ ባቀረቡት ፁኁፍ የብድር አቅርቦት ከኢኮኖሚ መዋቅር ጋር የተያየዘ ነው ብለዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የካፒታል እጥረት ያለበት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጌታቸው በበቂ ሁኔታ ሁሉንም ፍላጎት የሚያሟላ ካፒታል አለመኖሩን ገልፀዋል ፡፡
ለአብነት እ. ኤ.አ በ2022 /23 በሀገሪቱ የሚገኙ የገንዘብ ተቋማት በአጠቃላይ 1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር ብድር ሰጥተዋል ያሉት አቶ ጌታቸው ከዚህ ውስጥ 62 ነጥብ 4 በመቶ የሚሆነው ለግሉ ዘርፍ የቀረበ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ምንም እንኳን የብድር አቅርቦት መጠን እየጨመረ ቢመጣም የብድር አቅርቦቱና ፍላጎቱ የሚጣጣም አንዳልሆነ ገልፀዋል ፡ ፡
በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2020 በኢትዮጵያ ከአነስተኛ የብድር ተቋማት ጀምሮ ትልልቅ ባንኮች በጠቅላላ 6 ነጥብ 1 ሚሊየን የብድር ስምምነቶችን ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል ፡፡
ከዚህ ውስጥ 4 . 8 ሚሊየን የብድር ስምምነት በመፍፀም አነስተኛ የብድር ተቋማት ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል ነው ያሉት ፡፡
የብድር ስርጭቱን በተመለከተ አብዛኛው ብድር የተሰጠው አዲስ አበባ ላይ ነው ብለዋል፡፡
ይሁንና የብድር አቅርቦት ላይ እንደ ማዕድን ፣ ኢነርጅ እንዲሁም የሜካናይዝድ እርሻ ለማካካሄድ ከፍተኛ የብድር አቅርቦት ያለባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል ፡፡
ለብድር አቅርቦቱ ማነስ ኢኮኖሚው በቂ ካፒታል ማመንጨት አለመቻል አንዱ ችግር መሆኑን የገለፁት አቶ ጌታቸው ፤ በምክንያትነት ያስቀመጡት ባንኮች ገንዘብ የሚያሰባሰቡት ከደንበኞች ቀጠባ መሆኑን አመላክተዋል ::
የንግድ ባንኮች የብድር አቅርቦት አሰጣጥ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሄዎችን በተመለከተ ፁሁፍ ያቀረቡት ደግሞ የአዋሽ ባንክ ትራንስፎርሜሽን ዳሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ኃይሉ ናቸው ፡፡
አቶ ቴዎድሮስ ንግድ ባንኮች የሚሰጡት የብድር መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመሄድ ላይ ነው ብለዋል ፡፡
ይሁንና ባንኮቹ የሚሰጡት ብድር በዋናነት ንብረት ያላቸውን በመሆኑ አዳዳስ ቢዝነስ ለሚጀምሩ እና አነስተኛ ተባደሪዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም ብለዋል ፡፡
ባንኮች የሚያበድሩትን ገንዘብ በዋናነት የሚያሰባስቡት ከደንበኞች ተቀማጭ ነው በማለት የአቶ ጌታቸውን ሃሳብ አጠናክረዋል ፡፡ ንግድ ባንኮች አሁን ላይ ከደንበኞች የሚሰበሰቡት ተቀማጭ ከብድር ፍላጎት ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑን አሳይተዋል ፡፡
አሁን ላይ ባንኮቹ የሚሰበሰቡት ተቀማጭ 25 በመቶ ሲሆን የብድር ፍላጎቱ ደግሞ 27 በመቶ ነው ብለዋል ፡፡ ይህም ባንኮች የገንዘብ እጥረት እንዲገጥማቸው አድርጓል ብለዋል ፡፡
የልማት ባንክ የብድር አቅርቦት ተደራሽነት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በሚል የባንኩ ተወካዮች ወ/ሮ ማዕዛ ወልዴ እና አቶ ይልማ አበባ የባንኩን የብድር አስጣጥ በተመለከተ አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአጭር ፣ መካከለኛ እና ረጅም ጊዜ ብድር እንደሚሰጥ የጠቀሱት ወ/ሮ ማዕዛ ባንካቸው ፕሮጀክት እና ሊዝ ፋይናንስ ላይ በማተኮር ብድር መሰጠቱ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡
ልማት ባንክ ባለፉት አመታት ከነበረበት ውድቀት ለመውጣት ሪፎርም አድርጎ አሁን ላይ ትርፋማ በመሆን በለውጥ መንገድ ላይ ይገኛል ብለዋል ፡፡
አሁን ላይ ፍትሃዊ አሰራርን በመከተል ታዳጊ ክልሎች ላይ ትኩረት አድጎ እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለፁት ::
ልማት ባንክ እንደ ፖሊሲ ባንክነቱ ሌሎች ባንኮች በማይገቡበበት ዘርፍ ላይ ገብቶ ይሰራ ያሉት ወ/ሮ ማዕዛ በተለይ አበባና ግብርና ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርጎ መሰራቱ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡
የባንኩ ቺፍ ኦፍ ስታፍ አቶ ይልማ አበባ በበኩላቸው ባንካቸው 99 ነጥብ 9 በመቶ የግሉን ዘርፍ ብድር እንደሚያቀርብ ገልፀዋል ፡፡
ይሁንና ባንኩ ሰለሚሰጠው የሊዝ ፋይናንስ እና ፕሮጀክት ፋይናንስ አገልግሎት ደንበኞች ያላቸው ግንዛቤ አነሰተኛ መሆን ፣ ሊዝ ፋይናንስ ብድር ሳይሆን ኪራይ መሆኑን ያለማወቅ ፣ የማሽነሪዎችን አይነትና ጥራት አለማወቅ ጠቅሰዋል::
አክለውም ባንካቸው ትልልቅ ፕሮጀከቶችን ለማሰተናገድ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ትልቅ ፈተና እንደሆነበት አቶ ይልማ ገልፀዋል ፡፡
ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚቀርብን ብድር በተመለከተ ልማት ባንክ ላለፉት ሶስት አመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱንና ከስራና ክህሎት ሚንስቴር መስሪያ ቤት ጋር በመሆን ተጠቃሚ መሆን በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ፣ የባንክ ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡
የግሉን ዘርፍ አላሰራ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት የፖሊሲ ግብዓት እንዲሆኑ የአድቮኪሲ ስራ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን እስከ አመቱ መጠናቀቂያ ድረስ 14 የሚሆኑ የተመረጡ ዘርፎች ላይ የምክክር መድረክ እንደሚያዘጋጁ ዋና ፀሀፊዎ አቶ ሺበሺ ቤተ ማርያም ተናግረዋል ፡፡