የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ የግሉን ዘርፍ በማጠናከር ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጥና በመንግስትና በንግዱ ሕብረተሰብ መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ በመሆን እየሰራ ያለ አንጋፋ የንግድ ምክር ቤት ነው፡፡
ምክር ቤቱ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ከስምንት መቶ በላይ አባላቱ እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በኢንተር-ሌግዠሪ ሆቴል (በቀድሞው ኢንተርኮንትኔታል ሆቴል) መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም አካሂዷል ፡፡
በተካሄደው ጉባኤ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት፣ ም/ፕሬዚዳንትና የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን ግልጽ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ምርጫ ተከናውኖ አዳዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተመርጠዋል።
በዚህም መሰረት የአዲስ ቻምበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሆነው በ16ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ፣
1. ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ( የኒው ዳይሜንሽን የማኔጅመንት አማካሪ ኃ/የተ/ ሥራ አስኪያጅ) ………………………………………………………………………….ኘሬዝዳንት
2. አቶ ፋሲካው ሲሳይ ( የዲ ኤፍ ጂ ኮንስትራክሽን ስራ አስኪያጅ)……. ም/ ፕሬዝዳንት
3. አቶ መላኩ ከበደ ( የህብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ)…………….የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
4. አቶ ክብረት አበበ ( የጠብታ አምቡላንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ)……. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
5. አቶ አስፋው አለሙ ( የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ)…….. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
6. ወ/ሮ ሣራ ሰለሞን (የኢትዮ ሳሜል ኃ/የተ/ ሥራ አስኪያጅ)…. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
7. አቶ አበራ አበጋዝ (የኢዌይ ኖብል ኢንስፔክሽን ኤንድ ሰርቪስ ሥራ አስኪያጅ……… ………………………………………………………………………የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
8. ኢንጂ. አለማየሁ ንጋቱ (የኢኮን የህንፃ ተቋራጭ ኃ/የተ ሥራ አስኪያጅ……….. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
9. አቶ ሱለይማን ፈረጃ ( የዋይ-ኖት ኤሌክትሪክ እና የህንፃ መሳሪያዎች ሀላ/የተ ስራ አስኪያጅ) …የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
10. አቶ ግዛቸው ተከተለኝ ( ግዛቸው ተከተለኝ የተሳቢዎች መፈብረኪያ ስራ አስኪያጅ)….. ……የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
11. ኢንጂ. አበበ ጉርሜሳ (አበበ ጉርሜሳ ብረት እና እንጨት ሥራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ………………………………………………………………….. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል
መሆናቸውን በታላቅ አክብሮት እያሳወቅን አዲስ ቻምበር የግሉን ዘርፍ በማጠናከር በሀገሪቱ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የበኩሉን ሚና በይበልጥ እንደሚወጣ በዚሁ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
አዲስ ቻምበር፣የግሉ ዘርፍ አገልጋይ!!!!!