የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ለአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላት በሙሉ 

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ/ም በ ኢንተር ላግዠሪ ሆቴል / በቀድሞው ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል/ ከጠዋቱ 2፡3ዐ ጀምሮ 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡ ጉባኤው የ 2016 በጀት ዓመት የሥራ ክንውንን ይገመግማል፡፡ የውጭ ኦዲተሮች የሚያቀርቡትን ሪፖርት መርምሮ ያፀድቃል፡፡ ለቀጣዮቹ 2 አመታትም የሚያገለግሉ የፕሬዚዳንት፤የም/ፕሬዚዳንት እና የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትንም ይመርጣል፡፡ ሌሎች በጉባኤው የሚነሱ ጉዳዮችንም ያስተናግዳል ፡ ፡ በመሆኑም በዚህ ጉባኤ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ተገኝተው እንዲሳተፉ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ አባላት በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ቢሆን፣ ለዚሁ የተዘጋጀውን የውክልና ደብዳቤ የያዙ ህጋዊ ተወካዮች መላክ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ 

አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት