አዲስ ቻምበር ከ ኤስ ኤ ኬ የስልጠና እና የማማከር ድርጅት ጋር በመተባበር የሥራ መሪዎች መድረክ ፕሮግራምን አዘጋጅተዋል፡፡
መድረኩ ተጫባጭ ተሞክሮ ያላቸው መሪዎች በመድረኩ በመገኘት ለብዙ አመት ያካበቱትን ልምዳቸውን ያካፍላሉ፡፡
ፕሮግራሙ ጥር 21, 2018 ዓ.ም ከ11፡00- 2:00 ሰአት በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን በመድረኩ ተገኝተው ልምዳቸውን የሚያካፍሉት አንጋፋው የኢንሹራንስ መሪ አቶ ይሬድ ሞላ ናቸው፡፡
አቶ ያሬድ ሞላ የኒያላ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ማህበር ፕሬዚዳንት እንዲሁም የአፍሪቃ ኢንሹራንስ ድርጅት ሊቀመንበር በመሆን እያገለገሉ ያሉ አንጋፋ ኢትዬጵያዊ የኩባንያ መሪ ናቸው፡፡
ለበርካታ አመታት ድርጅትን በመምራት ስላጋጠማቸው ስኬት፣ የመሪነት መርሆቻቸቸው፣ ያጋጠሟቸው ተጋዳሮቶች እና እንዴት ችግሮችን አንደፈትዋቸው እንዲሁም ከልምዳቸው ተነስተው ለመሪዎች የሚያስተላልፉት መልእክት በንግግራቸው ውስጥ የሚዳሰሱ ናቸው፡፡
በመድረኩ ላይ በግል ተመዝግቦ መሳተፍ የሚቻል ሲሆን ማንኛውም ድርጅት የስራ አመራር ቡድኑን፣ የቦርድ አባላቶቹን አንዲሁም የወደፊት እጩ መሪዎችን በመድረኩ ላይ ማሳተፍ ይችላሉ፡፡
መድረኩን ስፖንሰር በማድረግ ምርት ወይም አገልግሎት ማስተዋወቅ ይቻላል ፡፡
በአሁኑ ወቅት በመሪነት ላይ የምትገኙ እንዲሁም ድርጅቶቻችሁን በእውቀት እና በጥበብ ለመምራት ለምታስቡ ሁሉ በመድረኩ በመገኘት ከአቶ ያሬድ ሞላ የካበተ ልምድ በመቅሰም ተጠቃሚ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል ።
ለመድረኩ ዝግጅት ወጪ መሸፈኛ 4000 ብር በሰው የሚከፈል ይሆናል፡፡ የመሪነት ብቃት ወሳኝ ነው።
ይደውሉ፣ ይመዝገቡ ።
0911194965/0911514422
_______________________________________________________________________________________________________________
Forum for Executive Leaders to host Mr. Yared Molla, CEO, Nyala Insurance Corporation as guest of honor.
Forum for Executive Leaders (FEEL), brings together prominent leaders and executives to share their leadership journeys, insights, and wisdom, fostering intergenerational transfer of knowledge and skills.
Call and Register at: 0911194965/0911514422
