ታላቅ የንግድ እድልና የገበያ ትስስር ለንግዱ ህብረተሰብ በኢስታንቡል ከአዲስ ቻምበር!!!!

በቱርክ ኢስታንቡል በተዘጋጀው 14ኛው የአለም የኢንደስትሪ ትብብር ፎረም( 14th Edition of the World Cooperation Industries Forum (WCIF) እና B2B ፕሮግራም ላይ የንግዱ ህብረተሰብ እንዲሳተፉ ስለመጋበዝ፤

እ.ኤ.አ. ከፌቡራሪ 11-12 2ዐ26 ድረስ በቱርክ ኢስታንቡል የሚካሄድ የቢዝነስ ፎረም (14th Edition of the World Cooperation Industries Forum (WCIF) እና የንግድ ለንግድ ውይይትና የገበያ ትስስር ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡

በፕሮግራሙ ላይም የተለያዩ አገራት ትላልቅ የንግድ ኩባንያ አመራሮችና የሀገራት ከፍተኛ መሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን የቢዝነስ ፎረሙ የሁለትዮሽ ንግድ ልውውጥ ለማድረግ ከመርዳቱም በላይ ከ1‚5ዐዐ በላይ ቢዝነስ ፕሮፌሽናልስ ቱርክን ጨምሮ ከአፍሪካ እንዲሁም ከተለያዩ አገራት በተለያየ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ፡፡

በመሆኑም በዚህ ጠቃሚ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

👉🏼 የአዲስ ቻምበር አባል የሆነ እና የአባልነት ክፍያ ያጠናቀቀ፤

👉🏼 የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም ባለቤት ወይም

👉🏼 በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ሀላፊ እና ባለሙያ ከሆኑ በድርጅቱ ፔሮል ላይ ተመዝግቦ በየወሩ የገቢ ግብር ወይም የሥራ ግብር ተቆርጦ ለገቢዎች ሪፖርት የተደረገበት እና የተከፈለበት ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፤

👉🏼 የፋሲሊቴሽን ክፍያ በሲ.ፒ.ኦ በAACCSA ስም ማሰራት

👉🏼 የጥቅል የተሳትፎ ክፍያ 75ዐ ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ብር ተቀይሮ ለመክፈል የሚመቻች እና ፋሲሊቴት የሚደረግ ሆኖ ይህም የሚያካትተው

📌የ4 ቀናት ባለ አራት ኮከብ የሆቴል ወጪ

# በኩባንያው እና ለተሳታፊው የግብዣ ደብዳቤ፣

📌 የሁለት ቀናት የመግቢያ ትኬት እና ያልተገደበ የቢቱቢ ፕሮግራሞች ላይ መሳተፍ፤

📌  የ2 ቀናት የቡና እና ሻይ ፕሮግራም፣

📌የGala Dinner፣ 📌በኢስታንቡል የጀልባ ጉዞ፣

📌  በኢስታንቡል የግዢ ጉብኝት፣

📌 የደርሶ መልስ ከአየር ማረፊያ እስከ ሆቴል እና ከሆቴል ፕሮግራሙ ቦታ የሚሸፈን

👉🏼  ለበለጠ መረጃ 0911212179 ደውለው ያነጋግሩ

አዲስ ቻምበር:የንግዱ ማህበረሰብ አገልጋይ !!!!

Video: https://web.facebook.com/reel/908188151745167

wpChatIcon
wpChatIcon