ምክር ቤቱ ያደረገው ድጋፍ ግምቱ ከ200 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ 240 ካርቶን ብሰኩት ለትምህርት ቤቱ ርዕስ መምህርት አሰረክቧል ፡፡
ድጋፉ በተደረገበት ወቅት የምክር ቤቱ ፕሬዘርዳንት መሰንበት ሽንቁጤ በትምህርት ቤቱ የሚደረገው ድጋፍ በዚህ ብቻ የሚያበቃ አይደለም ብለዋል፡፡
በቀጣይም ትምህርት ቤቱን ሌሎች የቦርድ አባላት እንደሚጎበኙት ጠቅሰው ንግድ ምክር ቤቱ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ገለፀዋል ፡፡
የምክር ቤቱ ዋና ፀሀፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም በበኩላቸው ንግድ ምክር ቤቱ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙና ኑራቸውን ጎዳና ላደረጉ ዜጎች ማዕድ በማጋራት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታውሰው ፤ የአጋዚያን ቁጥር አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቱን ለመደገፍ እየሞከረ ነው ብለዋል ፡፡
ይህ መጀመሪያ እንጅ የመጨረሻ አይደለም ያሉት አቶ ሺበሺ አጋዚያን ቁጥር አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትን ሞዴል በማድረግ ለሌሎች መሰል ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እንሚደረግ ገልጸዋል ፡፡
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወ/ሮ መሰረት ቦጋለ አጋዚያን ቁጥር አንድ የመጀመሪ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤቶች መካካል ግንባር ቀደም መሆኑን ፣ ተማሪዎችም በሰነ- ምግባር የታነፁ ናቸው ብለዋል ፡፡
ይህም ስሙ ከሳሪስ እና ኮተቤ አካበቢዎች ተማሪዎች መርጠውት የሚማሩበት ትምህርት ቤት መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ምንም እንኳን ትምህርት ቤቱ ከመንግስት በጀት ድጋፍ የሚደረግለት ቢሆንም ካሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንፃር በጀቱ በቂ አይደለም ብለዋል ፡፡
በተለይም የመፀዳጃና የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግሮች ፈተና እንደሆኑበት የገለፁት ርዕሰ መምህርቷ ወ/ ሮ መሰረት ተማሪዎች የሚጠጡትን ውሃ ከቤታቸው ለማምጣት ተገደዋል ብለዋል ፡፡
በመሆኑም ችግሮችን ለመቅርፍ ንግድ ምክር ቤቱ ድጋፋን በማጠናከር ከትምህርት ቤቱ ጎን እንዲቆም ጥሪያቸውን አቅረበዋል ፡፡
ወ/ሮ መሰንበት በበኩላቸው ምክር ቤቱ ግዙፍ ባንኮችንና የሚመሩ በቢዘንስ ዘርፍ አንቱታን ያተረፉ የዳሬክተሮች ቦርድ የሚመራ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ እነዚህ አባላት መጥተው እንዲጎበኙ በማድረግ ትምህርት ቤቱ ድጋፍ የሚያገኝበት ሆኑታ ይመቻቻል ብለዋል ፡፡
አጋዚያን ቁጥር አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተመሰረተ 63 ዓመት ያስቆጠረ አንጋፋ ትምህርት ቤት መሆኑን ሰምተናል ::