የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ፡ ለአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አባላት በሙሉ

አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ/ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ከጠዋቱ 2፡3ዐ ጀምሮ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡

ጉባኤው የ2015 በጀት ዓመት የሥራ ክንውንን ይገመግማል፡፡ የውጭ ኦዲተሮች የሚያቀርቡትን ሪፖርት መርምሮ ያፀድቃል፡፡ በመሆኑም በዚህ ለምክር ቤታችን የወደፊት እርምጃ እጅግ ወሳኝ በሆነ ጉባኤ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሥራ አስኪያጅ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ተገኝተው እንዲሳተፉ የአክብሮት ጥሪያችንን እያቀረብን የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሥራ አስኪያጅ በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ቢሆን፣ ለዚሁ የተዘጋጀውን የውክልና ደብዳቤ የያዙ የድርጅትዎን ባልደረባ መላክ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

 

አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት

ለተጨማሪ መረጃ፣

በስልክ ቁጥር 011 5513814፣ 5519817፣5514517፣5528205፣ 5518055 የውስጥ መስመር 214/222/202 በመደወል የምክር ቤቱን ባልደረቦች ማነጋገር ይቻላል፡፡