ለደረቅ ወደብ ልማት እና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ብቃትን ለማረጋገጥ የወጣ መመሪያ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነሐሴ 2011 ዓ.ም. ባፀደቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎጂስቲክስ ስትራቴጂ፣ በደረቅ ወደብ ልማት እና አገልግሎት ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችል የፈቃድ አሠጣጥ ሥርዓትን ማሻሻል እንደ አንድ የስትራቴጂ ማስፈፀሚያ ስልት በማድረግ እንደ አቅጣጫ ማስቀመጡ፤
በደረቅ ወደብ ልማት እና አገልግሎት ዘርፍ ላይ መሠማራት ለሚፈልጉ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ
ባለሃብቶች የፍቃድ አሠጣጥ ሂደት ላይ የብቃት ማረጋገጫ የሚሰጥበትን ሥርዓት እና የምዘና ሂደት
እንዲሁም ይህ አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ መወሰን በማስፈለጉ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዝያ 29/2012 ባደረገው 20ኛ አስቸኳይ ስብሰባባ ባፀደቀው የሎጂስቲክስ
ዘርፍ ፖሊሲ እና በኢንቨስትመንት ደንብ ቁጥር 474/2020 በአንቀጽ 6 መሠረት የደረቅ ወደብ ልማትና
አገልግሎት ለግል ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆን የተወሰነ በመሆኑ፤ለደረቅ ወደብ ልማት እና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ብቃትን ለማረጋገጥ የወጣ መመሪያ DPD-final-version-14