የኢትዬ_ ዱባይ የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ ።

በአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/አዲስ ቻምበር/፣ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዬጲያ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ኤምባሲ፤  በዱባይ ቻምበር  ፣በተባበሩት አረብ ኢምሬት የኢትዬጲያ ኤምባሲ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የጋር ትብብር የተዘጋጀው የኢትዬ ዱባይ የንግድ ፎረም በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሂዷል፡፡

የንግድ ፎረሙ ላይ ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ከአዲስ ቻምበር ፣ ከዱባይ ቻምበር ፣ የሁለቱ ሐገራት ኤምባሲዎች እና ሌሎችም አመራሮች መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በዚህ የቢዝነስ ልኡክ ላይ ከዱባይ የመጡ በታዳሽ ኀይል፤ በማኑፋክቸሪንግ ፣በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፤በህክምናና በፋርማሲ ፤በምግብና በመኪና መገጣጠም ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በአዲስ አበባ በመገኘት ምርቶቻቸውን እና አገልግሎታቸውን አስተዋውቀዋል።

የዱባይ ታዋቂ ኩባንያዎች ከሀገር ውስጥ ተመሳሳይ ኩባንያዎች ጋር የቢዝነስ የልምድ ልውውጥና ትስስር  አድርገዋል፡፡

በኮንፈረሱ ላይ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት(አዲስ ቻምበር) ምክትል ፕሬዝዳንት ኢንጂነር አበበ ጉርሜሳ ባስተላለፉት መልእክት የሁለቱ ሐገራት የንግድ ልውውጥ በስፋት እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው የዱባይ ባለሐብቶች ትኩረት በተሠጣቸው ዘርፎች በኢትዬጲያ እንዲሰማሩ አዲስ ቻምበር ከዱባይ ቻምበር ጋር ተባብሮ ይሠራል ብለዋል።

በፎረሙ ላይ ከ400  የሚጠጉ የአዲስ ቻምበር አባል ኩባንያዎች ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት የንግድ ልውውጥ መጠን እኤአ በ 2025 ከ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ መድረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

አዲስ ቻምበርና ዱባይ ቻምበር እኤአ በ2024 ንግድና ኢንቨስትመንትን በጋራ ለማስፋፋት የጋራ መግባቢያ ሠነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።

አዲስ ቻምበር፤ ላለፉት 79 አመታት የንግዱ ማህበረሰብ አገልጋይ

#addischamber

wpChatIcon
wpChatIcon