7ዐ አመታት እድሜን ያስቆጠረው አንጋፋው የአዲስአበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት በአዋጅቁጥር 341/1995 በአዲስ መልክ ከተደራጀ ወዲህ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአመት አንድ ጊዜ ያካሂዳል፡፡ በዚህም መሠረት 13ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ሐሙስ መስከረም 25 ቀን 201ዐ ዓ/ም በአዲሡ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ያካሂዳል፡፡
ጉባኤው የ2009 በጀት ዓመት የሥራ ክንውንን ይገመግማል፣ የውጪ ኦዲተሮች የሚያቀርቡትን ሪፖርት መርምሮ ያፀድቃል፣ በተከናወኑ አበይት ተግባራቶች ዙሪያም የምክር ቤቱ አባላት ውይይት ያካሂዳሉ፡፡በመሆኑም የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ በጉባዔው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል ፡፡