የኢትዮ- ሞሮኮ የኢኮኖሚ ጉባኤና ኢግዚቢሽን በአዲስ አበባ ተካሄደ።

በዛሬው እለት የተጀመረው የኢትዮ – ሞሮኮ የኢኮኖሚ ጉባኤና ኢግዚቢሽን የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፤የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፤ የአዲስ ቻምበር ዋና ጸሀፊ ( መሰረት ሞላ ዶ/ር) ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፤ የንግድ ምክር ቤቱ አባላት፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የመገናኛ ብዙኃንን በአንድ መድረክ ያሰባሰበ ነበር፡፡

የኢትዮ- ሞሮኮ የቢዝነስ ጉባኤና ኢግዚቢሽን “Harnessing Impact South South Cooperation” የሚል መሪ ቃል ያነገበ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጠነከረ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳያና ውጤት ነው ያሉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ኤርጎጌ ተስፋዬ( ዶ/ር) ናቸው፡፡

ሚኒስትሯ አክለው እንዳሉት ኢትዮጵያና ሞሮኮ በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የእርስ በእርስ ንግድ ግንኙነት በመምራት ፈር ቀዳጅ መሆናቸውን በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሚኒስትሯ የሞሮኮ ኤምባሲና የሚኒስትር መስሪያ ቤታቸው ይህን ወቅታዊና ወሳኝ የቢዝነስ ጉባኤ በማካሄድ ላበረከቱት አስተዋጾ ምስጋናቸውን ችረዋል፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ ነቢላ ተቦር የ BADEE, Innovx Branch, OCP ግሩፕ ዋና ዳይሬክተር በሁለቱ ሀገራት የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትና ስራ ፈጣሪዎች ግንኙነታቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ካላቸው እምቅ የኢኮኖሚ አቅም ጋር ሲነጻጸር በንግድና ኢንቨስትመንት ዙርያ ሰፊ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው በጉባኤው ላይ ተጠቁሟል፡፡