የኢትዮጵያ ቻምበር እና የአዲስ ቻምበር ለግሉ ዘርፍ ልማት በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። 

የሁለቱም ንግድ ምክር ቤት ፕሬዚደንቶች በቀጣይ በጋራ መሰራት በሚገባቸው አንኳር ጉዳዬች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ ጋር ነው በጽሕፈት ቤታቸው የተወያዩት፡፡

በውይይቱም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባል ምክር ቤቶችን ለማጠናከርና በጋራ መሰራት ባለባቸውን ጉዳዮች ዙሪያ አብራርተዋል፡፡

አባል ምክር ቤቶች እንዲጠናከሩ ለማስቻል ተቀራርቦ መሰራት ይገባል ያት አቶ ሰብስብ የአሰራር ሂደቶችን በማስተካከል በንግዱ ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ በበኩላቸው ሁለቱ ምክር ቤቶች በመቀራረብ እና በመደጋገፍ መስራት እንዳለባቸው በማንሳት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እያደረገ ያለው ድጋፍም የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የምክር ቤቶቹን አቅም በሚያሳድጉ እና በሀገራዊ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ሪፎርም ተግባራዊ በማድረግ የአባል ምክር ቤቶችን አቅም በማሳደግ እና የንግዱን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ አሰራሮችን እየተተገበረ መሆኑም የሚታወቅ ነው፡፡

wpChatIcon
wpChatIcon