ከተመሠረተ 18 ያህል ወራትን ያስቆጠረው የሸገር ከተማ ንግድ ም/ቤት ከአንጋፋው አዲስ ቻምበር በርካታ የአሠራር፤ የአወቃቀር የአተገባበር ልምዶች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በአድቮኬሲ፤በአባላት ልማት፤በፕሮጀክት እና ትብብር ፤በሚዲያ እና በኮሚኒኬሽን አሠራር እና ሪፖርት አደራረግ ሥርዓት ላይ የአዲስ ቻምበር የመምሪያ ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የ 77 አመቱ አዲስ ቻምበር በተለይ የንግዱ ሕ/ሰብ የሚያጋጥሙት ተለዋዋጭ መዋቅራዊ እና የፖሊሲ ችግሮችን ተከታትሎ ጥናቶችን በማድረግ መንግሥት የሕግ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ለአመታት ያደረገው እንቅስቃሴ ለሸገር ንግድ ም/ቤት ሰፊ ልምድ ያስችለዋል ተብሏል፡፡ የሸገር ንግድ ም/ቤት ቦርድ አባላት በበኩላቸው በተደረገላቸው ማብራሪያ ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸው በተገኘው ልምድ ንግድ ም/ቤታችን ለማጠናከር ሰፊ ግብአት በማግኘታቸው ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ ከአዲስ ቻምበር ጋር ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እና በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምነት ለመፈራረም ፍላጎት እንዳላቸው ጨምረው ገልጸዋል፡፡