የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ እና አጋሩ የአዲስ አበባ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በኩባንያ መልካም አስተዳደር/ ኮርፖሬት ገቨርናንስ/ ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ላይ ተሳተፉ፡ ፡
ስልጠናው ከዓለም ዘመናዊ እና ተለዋዋጭ ንግድ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚሄድ የንግድ ምክር ቤት መሪዎችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት እጅግ አስፈላጊ እና ወቅቱ የሚጠይቀው መሆኑን የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡ ፡
በዚህ ረገድ አዲስ ቻምበር የምክር ቤቱንም ሆነ የተለያዩ ኩባንያወዎች የቦርድ አባላትን ተከታታይነት ባለው ሁኔታ በኩባንያ መልካም አስተዳደር ዙሪያ አቅማቸው እንዲጎለብት ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡ ፡
ስልጠናው በቅርቡ አዲስ ለተመረጡት የንግድ ም/ቤቶቹ የቦርድ አበላት የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናውም በኩባንያ መልካም አስተዳደር (Corporate Governance) ጽንሰ ሃሳብ፤ተግዳሮቶች፤ የመፍትሔ አሰጣጥ ስልቶች፣ እንዲሁም የተቋማት የአሰራር ፖሊሲዎች፤ማንዋሎች፤ የቦርድ አባላት ሃላፊነቶች እና ግዴታዎች፤ተቋማዊ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ሥርዓት መዘርጋት በሚሉ ነጥቦች ላይ ያተኮረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ስልጠናው ስለ ካፒታል ገበያና የአሠራር ሂደት፤ ንግድን ከሥጋት የመከላከል ስልቶች በስልጠናው የተካተቱ ሲሆን የቀድሞዋ የኢትዮጵያ የንግድ ም/ቤት ፕሬዝደንት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ለቦርድ አባላቱ ልምዳቸውን ማካፈላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
