የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት እያከበረ ነው። በወቅቱ የአዲስ ቻምበር 75 ዓመት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን በስካይላይት ሆቴል ተመርቆ ተከፍቷል። ኤግዚቢሽኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድና የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ ከፍተውታል። የፎቶ ኤግዚቢሽኑ ላይ 156 ፎቶዎች ለዕይታ ቀርበዋል። የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የፋሺስት ወረራ ካበቃ በኋላ በ1939 ዓ.ም የንግዱን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተቋቋመ ምክር ቤት ነው።