አዲስ ቻምበር ከዳካር አቻው ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ

አዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት / አዲስ ቻምበር/ ከሴኔጋሉ የዳካር ንግድ ኢንዱስትሪ እና ግብርና ምክር ቤት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ የመግባቢያ ሰሰድ ተፈራረመ፡፡
ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚገኙ የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን እና መረጃዎችን ከመጠቀም ባለፈ በሁለቱ ሀገራት የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ተቀራርበው እንዲሰሩ ያስችላል ተብሏል፡፡
ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት እና ሚስተር ኣብዱላሂ ሶው የዳከር ንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የዳካር ንግድ ማህበረሰብ ባለበት ስምምነቱን ተፈራርመዋል፡ ፡
ሁለቱም ፕሬዚዳንቶች በተፈራረሙበት ወቅት እንዳስታወቁት ይህ ስምምነት የቢዝነስ ትስስር እንዲጠናከርና መልካም እድሎችን ለመጠቀም ያስችላል ብለዋል፡፡
በፕሬዚዳንት መሰንበት ሸንቁጤ የሚመራውን የአዲስ ቻምበር የልኡካን ቡድንን በዳካር የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ መላኩ ለገሰ ተቀብለውታል፡ ፡
አምባሳደር መላኩ ለገሰ በጋራ መግባቢያ ሰነድ ስምምነቱ ወቅት እንደተናገሩት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ታሪካዊና ረጅም አመትን የዘለቀ መሆኑን ተናግረው እንዲህ አይነት ስምምነት ግንኙነቱን በኢኮኖሚ እንዲጠናከር የሚያስችል ነው ብለዋል፡ ፡
የአዲስ ቻምበር ልኡካን ቡድን በሴኔጋል ዳካር ቆይታው የተለያዩ ተቋማትን የሚጎበኝ ሲሆን ከነዚህ መካከል የሴኔጋል ካፒታል ገበያ፤ የሴኒጋል ኢንዱሰትሪ ፓርክ፤ የሴኔጋል የኢንቨስትመንት ቢሮ እና አለም አቀፍ የግል ኢንቨስትመንት ባንኮች ዋነኞቹ ናቸው፡ ፡