የአዲስ ቻምበር ፕሬዝደንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ እና ዋና ጸሐፊው መሠረት ሞላ(ዶ/ር) ከማሌዥያ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ሚኒስቴር ሃላፊዎች ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ወ/ሮ ዘሃራ እንዳረጋገጡት በሁለቱ አገራት መካከል ሰፊ የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ ዕድሎችን ለመጠቀም አዲስ ቻምበር ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል ።
የማሌዢያ የንግድ ኮሚሽነሩ ያዝሪን ስያከሪ በበኩላቸው ከአዲስ ቻምበር ጋር በመተባበር የሁለቱን ወገኖች የግል ዘርፍ በኢንቨስትመንት፤ ንግድና የገበያ ዕድሎችን ለማስፋት በጋራ ለመስራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ የማሌዥያ ትልቅ የንግድ ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ የሚመጣ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የአዲስ አበባ የንግዱ ህብረተሰብ የእርስ በእርስ የንግድ ለንግድ ውይይት የሚያደርግ ይሆናል።
