አርጀንቲና በምግብ ማቀነባበርና ፣ መጠጥ እና ግብርና ቴክኖሎጅ ዘርፍ ምርቶቿን ወደ ኢትዮጵያ ገቢያ ይዛ መግባት እንደምትፈለግ ተገለፀ፡፡

ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የአርጀንቲና አምባሳደር ሮኪቲያሊያቲ ኤግናሲዮ ለኢትዮጵያዊያን የቢዝነስ ማህበረሰቦች ሀገራቸው በግብርናው ዘርፍ ሰላላት አምቅ አቅም እና እንዴት በጋራ መስራት እንችላለለን የሚለውን በገለፁበት ወቅት ነው ፡፡ በኢትዮጵያና አርጀንቲና መካከል ያለውን ንግድና እና ኢንቨስትመንት ማሳደግ ያስፈልጋል ያሉት አምባሳደሩ ፤ ለዚህም ኢምቢያሳቸው ዝግጅ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡ በምግብ ፣ በመጠጥና የግብርና ማሽነሪዎች ትኩረት አድርጋ መሰራት እንደምትፈልግም ነው አምባሳደር ኤግናሲዮ የገለፁት ፡፡ የአኩሪ አተር ፣ በቆሎ ፣ ስጋ ፣ ማሽላ ፣ የሱፍ ዘይት እና የወይን መጠጥ ምርት በከፍተኛ መጠን በማምረት ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሾች መሆናቸውንም ነው የገለፁት ፡፡ የሱፍ አበባ ዘይት በማምረትና በመላክ እንዲሁም በወይን መጠጥ በማምት በዓለም ውስጥ አምስት አገሮች መካከል አንዷ መሆኗንም አምባሳደር ኤግናሲዮ ጠቅሰዋል ፡፡ በጋራ በመነገድ እኩል ተጠቃሚ መሆን የሚያስችለንን ስራ ለመስራት ኢምባሲያቸው ዝግጁ ነው ብለዋል ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች በሁለቱ አገራት ስላላው እምቅ አቅም እና እንዴት መሰራት አለበት የሚለውን ጥያቄ አንሰተው አምባሳደሩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል ፡፡ በተለይ በቀጣይ የካቲት ወር ላይ በግብርናና ምግብ ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ለማየትና በጋራ መሰራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር የኢትዮጵያን ነጋዴዎች ንግድ ሉዕክ ይዞ ለመሄድ ማቀዱን ሰምተናል ፡፡

wpChatIcon
wpChatIcon