የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡
የዘርፍ ማህበራት በተቋቋመት የህግ አግባብ መሰረት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ
ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ገልጸዋል፡፡
መንግስት ከዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ያደነቁት የዘርፍ ማህበራቱ ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ተገቢው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
መንግስት በዋናነት ለአምራቾች ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ከተማ አስተዳደሩ ዘርፉን ለማሳደግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ እና ክትትል እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ከመንግስት የሚጠበቁ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ገልጸው አምራቾች እንደ ሀገር የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸው ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል፡፡
