ታዋቂው የቱርክ የአልባሳት ኩባንያ ኬሳስ(KSAS) በኢትዮጵያ መዋእለ ነዋዩን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።

በአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት የተመራ የንግድ ልኡካን ቡድን የኩባንያውን እንቅስቃሴ በኢስታንቡል በመጎብኘት ውይይት አድርጓል ።

የቱርኩ አለም አቀፍ ዝና ያለው ግዙፉ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ኩባንያ በኢትዮጵያ በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ለአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ገልጿል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ገበያ እንዲቀላቀል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አዲስ ቻምበር ድጋፍ እንዲያደርግለት ጠይቋል።

ከ 80 ሀገራት በላይ ምርቱን እንደሚልክ የገለፀው ይሄው ታዋቂ ኩባንያ በኢትዬጵያ ምርቱን ለማምረት ፍላጎት እንዳሳደረ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ( አዲስ ቻምበር) ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሐራ መሐመድ እንደገለፁት ኩባንያው በኢትዮጵያ መዋእለ ነዋዪን እንዲያፈስ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቷ እና የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት በቱርክ ኢስታንቡል ተገኝተው ከኩባንያው ሀላፊዎች ጋር በኢንቨስትመንት መርሃ ግብሩ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ወቅት የኬሳስ አልባሳት ኩባንያ አመራሮች የኢንቨስትመንት ዕቅዳቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ዘመናዊ የማምረቻ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ለመገንባት ኩባንያቸው ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አዲስ ቻምበርም ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር ኩባንያው የኢትዬጲያን ገበያና ቢዝነስ እንዲቀላቀል ድጋፍ ይደረጋል ተብሏል።

የአዲስ ቻምበር የንግድ ልኡካን በ14ኛው የአለም ኢንዱስትሪ ትብብር የቢዝነስ ፎረም ላይ በኢስታንቡል የተሳተፈ ሲሆን ከኢስታንቡል ንግድ ምክር ቤት እና ከተለያዩ ግዙፍ አለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የኢንቨስትመንት ውይይት አድርጎ ተመልሷል።

ስመጥሩ ኬሳስ የአልባሳት ኩባንያ በምስራቅ አውሮፓ ፣ በሩሲያ፣ በሰሜን አፍሪካ ፣በመካከለኛው ምስራቅ እና በሩቅ ምስራቅ ሰፊ ገበያ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል ።

wpChatIcon
wpChatIcon