በአዲስ አበባ ዘርፍ ም/ቤት ከህዳር 12-16 2017 ለሚካሄደው የአዲስ አውቶሞቲቭ ንግድ ትርኢት እና ኤክስፖ የፓናል ውይይት ተደረገ ::

በፓናል ውይይቱ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን አዲስ አውቶሞቲቭ ንግድ ትርኢት እና ኤክስፖ” በቢዝነስ ትስስር እና ትብብር የሀገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ የአውቶሞቲቭ ዘርፍ እና ተዛማጅ ኢንዱስትሪዎችን በማስተዋወቅ ረገድ ያልው ሚና በዝርዝር ቀርቧል ።
ዝግጅቱ የእውቀት፣ ክህሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማመቻቸት፣ ፈጠራን ለማዳበር፣ የስራ እድል ለመፍጠር እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎችን ለመፍጠር ያለው ሚና በሰፊው የተነሳ ሲሆን ባልድርሻ አካላትም ውይይት አድርገውበታል::