ይህ የተባለው አዲስ ቻምበር ከኢንቨስትመንት ክላይሜት ሪፎርም ጋር በጋራ ባዘጋጁት የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡ በንግድና በተለያዩ ቢዝነስ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ለሀገር ኢኮኖሚና ለስራ እድል ፈጠራ የሚያበረክቱት አስተዋጾ ጉልህ ቢሆንም በርካታ ተግዳሮቶች እንዳሉባቸው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡
ከነዚህም መካከል ስር የሰደደ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና፤የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፤የመሬት አቅርቦት ችግር፤ የክህሎት ክፍተት እንዲሁም የመስሪያ ቦታ ችግሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ችግሮች ምላሽ እንዲያገኙ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዲስ ቻምበር ከልማት አጋሮች ጋር አንድ ላይ በመሆን ሴቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ውስጥ ገብተው ስኬታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ጥረቶች መካከል ምክር ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች የጾታ እኩልነትን ማእከል ያደረጉ እንዲሆኑ የማድረግና እየሴቶችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ይበልጥ ማስፋፋት ይገኝበታል፡፡
በተካሄው የውይይት መድረክ ላይ ከተለያዩ የቢዝነስ ተቋማት የተውጣጡ ተሳታፊዎች ከአገልግሎት አሰጣጥ ፤ከፋይናንስ ተደራሽነት አንጻር የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን እንዲሁም በቀጣይ በምክር ቤቱ አማካኝነት አገልግሎቶች ሰፋ ያለ ግብአት ቀርቧል፡፡ ይህ መድረክ የምክር ቤቱን አገልግሎት ጾታን ማእከል ባደረገ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ ፤የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት፤ በምክር ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች የሴት ስራ ፈጣሪዎችን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ለማቅረብ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡