ለ2 ቀናት በኢስታንቡል ሲካሄድ የነበረው 14ኛው የአለም የኢንዱስትሪ ትብብር የቢዝነስ ፎረም በስኬት ተጠናቀቀ ።

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ነጋዴ አባላትና አመራሮች ትልቅ የንግድ ትስስርና ተቋማዊ አጋርነት የፈጠሩበት መድረክ መሆኑም ተመላክቷል።

14ኛው የአለም የኢንዱስትሪ ትብብር የንግድ ፎረም የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንትና አመራሮችን ጨምሮ የሀገራት ሚኒስትሮች ፤ የተለያዩ ሐገራት ንግድ ምክር ቤት አመራሮችና አምባሳደሮች እንዲሁም ከ 1500 በላይ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዬችን አስተናግዷል ።

አዲስ ቻምበር እና የልኡካን ቡድኑ የኢትዬጵያን እና የአዲስ አበባን የንግድና ኢንቨስትመንት አቅምና አማራጮች በስፋት አስተዋውቀዋል ።

የቱርክም ሆነ የሌሎች ሐገራት ባለሐብቶች በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ መዋእለ ነዋያቸውን በፈለጉት የኢኮኖሚ ዘርፍ እንዲያፈሱና ትርፋማ እንዲሆኑ አዲስ ቻምበር ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ኩባንያዎቹ ወደ ተጨባጭ ስራ እንዲገቡ አዲስ ቻምበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የማመቻቸት ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል ።

የአዲስ ቻምበር ልኡካን ቡድን ከቢዝነስ ፎረሙ ጎን ለጎን መሠል ከሆኑ አቻ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የሁለቱን ከተሞች የንግድ ሁኔታ ይበልጥ በሚያድግበት ዙሪያ ውይይት አድርጓል ።

አዲስ ቻምበርና የኢስታንቡል ንግድ ምክር ቤት ረጅም አመታትን ያስቆጠረ አጋርነት እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል ።

ቱርክና ኢትዬጲያ በንግድና በዲፕሎማሲ ያላቸው ትስስርና ግንኙነት እንዲሁ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ እና ጠንካራ መሆኑም ተመላክቷል።

wpChatIcon
wpChatIcon